በውጪ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን የቀረቡ የብድር አገልግሎቶች!

1.     ለግል ጉዳዮች/ ፍጆታ የሚውል  ብድር

ይኽ አገልግሎት የገንዘብ ፍጆታቸው መጠነኛ ለሆኑ የተለያዩ የግል ጉዳዮች የሚውል የገንዘብ መጠን በብድር መልክ የሚቀርብበት የብድር አይነት ሲሆን፤ ለምሳሌ ለቤት እቃ መግዣ፣ ለቤት ወይም ለመኪና ማደሻ፣ ለትምህርት፣ ለህክምና፣ ለሠርግ እና መሰል ጉዳዮች ማስፈፀሚያ የሚሰጥ የብድር አይነት ነው፡፡

በአገልግሎቱ ለመጠቀም መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-

·       ሕጋዊ የሆነ የትውልድ ኢትዮጵያዊያን የውጪ ዜጋ መታወቂያ፣

·       ተመጣጣኝ የሆነ የብድር ማስያዣ በባንኩ የብድር መመሪያ መሰረት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤ለምሳሌ በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያለ የአክሲዮን ባለቤትነት ሠርተፍኬት ወይም የባንኩ የብድር ሕግ በሚያዘው መሠረት ተቀባይነት ያለው ቋሚ ሀብት፣ እንዲሁም

·       ብድሩን ለመውሰድ ባንኩ ያስቀመጠውን የገንዘብ መጠን ያህል በውጪ ምንዛሪ (በዶላር፣ በፓዎንድ ወይም ዩሮ) ማስቀመጥ፣

ብድሩ ለቤት ዕቃ መግዣ የሚውል ከሆነ ገንዘቡ በቀጥታ ዕቃውን በቀጥታ ለሚያቀርበው ድርጅት የሚተላለፈ ሲሆን፣ ብድሩ ተከፍሎ የሚያልቅበት ጊዜ ከ5 ዓመት በላይ መብለጥ አይኖርበትም፡፡ 

 

2.   ለመኪና መግዣ የሚውል ብድር ይኽ የብድር አይነት ከተመረቱ 15 ዓመታት በላይ ያልሆናቸው ኮድ 2 የግል አውቶሞቢሎችን ወይም ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ኮድ 3 መኪኖችን ለመግዛት የሚያስችል የብድር አይነት ነው፡፡  

በአገልግሎቱ ለመጠቀም መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-

·       ሕጋዊ የሆነ የትውልድ ኢትዮጵያዊያን የውጪ ዜጋ መታወቂያ፣

·       ብድሩን ለመውሰድ ባንኩ ያስቀመጠውን የገንዘብ መጠን ያህል በውጪ ምንዛሪ (በዶላር፣ በፓዎንድ ወይም ዩሮ) ማስቀመጥ፣

·       የሚገዛው መኪና ለብድሩ በማስያዣነት የሚያዝ ሲሆን፤ ሆኖም በተበዳሪው የባንክ ሒሳብ የተቀመጠው የውጪ ምንዛሪ መጠን ከሚጠበቀው አነስተኛ ወሰን ያነሰ ሆኖ ከተገኘ በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያለ የአክሲዮን ባለቤትነት ሠርተፍኬት ወይም የባንኩ የብድር ሕግ በሚያዘው መሠረት ተቀባይነት ያለው ቋሚ ሀብት በተጨማሪ ማስያዣነት የሚወሰድ ይሆናል፡፡

 

3.     ለቤት መግዣ የሚውል ብድር

ሕብረት ባንክ የዲያስፖራውን ፍላጎት በማከለ መልኩ ለቤት መግዣ ወይም መስሪያ የሚውል የብድር አገልግሎት ያቀርባል፡፡  

በአገልግሎቱ ለመጠቀም መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-

·       ሕጋዊ የሆነ የትውልድ ኢትዮጵያዊያን የውጪ ዜጋ መታወቂያ፣

·       የአጠቃላይ ብድሩን 20 በመቶ ያህል በውጪ ምንዛሪ (በዶላር፣ በፓዎንድ ወይም ዩሮ) ማስቀመጥ፣

·       በራስ አቅም ለሚገነባ የግል ቤት ከተበዳሪው የሚጠበቀው የመዋጮ መጠን የሚጀምረው የቤቱ የግንባታ መጠን 20 ወይም 30 በመቶ መድረሱን በምህንድስና ክፍል ከተረጋገጠ በኋላ   ይሆናል፣

·       የብድሩን ክፍያ ለመጀመር የ18 ወራት የችሮታ ጊዜ የሚኖር ሲሆን፤ በዚህ ወቅት የሚጠራቀመው የወለድ መጠን በየወሩ መቃለል ይኖርበታል፡፡ ይህንን ወለድ ለመክፍል የብድር ስምምነቱ በሚያዘው መሰረት በብር ወይም በውጪ ምንዛሪ መክፈል የሚቻል ሲሆን፤ ይህም በስምምነቱ ላይ በግልፅ መስፈር ይኖርበታል፡፡

·       የብድር ማስያዣን በተመለከተ ለመኖሪያ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚገነባው ወይም የሚገዛው ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ለብድሩ መያዣነት ይውላል፡፡ ሆኖም ቤቱ በባለቤትነት የተያዘው በቤት አልሚ ድርጅት ወይም በቤት ሥራ ማኅበር ከሆነ ወይም ቤቱ ተጠናቆ የባለቤትነት መብቱ ወደ ገዢው የሚተላለፍበት ጊዜ ረዥም ከሆነ ተጨማሪ ቋሚ ንብረቶች ወይም የአክሲዮን ባለቤትነት ሠርተፍኬት ለማስያዣነት ያስፈልጋሉ፡፡

 

 

4.     የዲያስፖራ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ብድር

ሕብረት ባንክ ለንግድ ሥራ መጀመሪያ ወይም ማጠናከሪያ የሚውል ብድር ለዲያስፖራው የሚያቀርብ ሲሆን፤ የብድሩ አይነትም በቀጥታ ንግዱን በባለቤትነት ለሚመራው ዲያስፖራ የሚሰጥ ወይም ዲያስፖራው በባንኩ በሚያስቀምጠው የውጪ ምንዛሪ መሠረት ለቤተሰብ ወይም ለንግድ ሸሪኮች የሚሰጥ የብድር አይነት ነው፡፡ በዚህ መልኩ የሚሠጡ የብድር አይነቶች ለሚከተሉት የንግድ ሥራ አይነቶች ሊውል ይችላል፡-

·       በቤት አልሚነት (Real Estate) ዘርፍ ለተሰማሩ የሚውል ብድር- በዚህ ዘርፍ ውስጥ ዳያስፖራው ለንግድ አገልግሎት ወይም ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት በውጭ ምንዛሬ በመቆጠብ ለሚሰራው ስራ የሚውል የሚውል የብድር አገልግሎት ነው፡፡  

·       በኢንዱስትሪ  (Manufacturing) ዘርፍ ለተሰማሩ የሚውል ብድር - በዚህ ዘርፍ ውስጥ ዳያስፖራው ለኢንዱስትሪ አገልግሎት በውጭ ምንዛሬ በመቆጠብ ለሚሰራው ስራ የሚውል የብድር አገልግሎት ነው፡፡ 

·       የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሠጡ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም ለኮንስትራክሽን አገልግሎት የሚከራዩ ማሽኖችን በከፊል ወጪ ለመሸፈን የሚሰጥ የብድር አገልግሎት - በዚህ ዘርፍ ውስጥ ዳያስፖራው ለተለያዩ አገልግሎቶች ለሚውሉ ተሸከርካሪዎች እና ለኮንስትራክሽን አገልግሎት የሚከራዩ ማሽኖችን ለሚሰሩት ስራ የሚውል የብድር አገልግሎት ነው፡፡ 

 

ለሁሉም  የብድር አይነቶች ተበዳሪዎች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

ü  ሕጋዊ የሆነ የትውልድ ኢትዮጵያዊያን የውጪ ዜጋ መታወቂያ፣

ü  ተበዳሪው በአገር ውስጥ ብድር ለመውሰድ የሚያስችል  በቂ የንግድ ልምድ ያለው፣

ü  የብድር ማስያዣን በተመለከተ ለሁሉም የስራ ዘርፎች ንግዱ በራሱ ዋስትና ሊሆን የሚችል ሲሆን፤ ሆኖም ግን የንግድ የስራ ዘርፉ በቂ ካልሆነ ተጨማሪ ቋሚ ንብረቶች ወይም የአክሲዮን ባለቤትነት ሠርተፍኬት ለማስያዣነት ያስፈልጋሉ፡፡

 

Click Here to find Diaspora Saving Deposit Account  Opening Application Form