ሚያዝያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከለሊቱ 6 ሰዐት በመስቀል ፍላዎር ቅርንጫፋችን ላይ የዘረፋ ጥቃት ሙከራ መቃጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

የባንኩ የጥበቃ ሰራተኛ አቶ ተመስገን ከሮከፖሊስ ባልደረቦች ጋር በመሆን በዕለቱ በውጪ ድርጅት በኩል በቅርንጫፉ ተቀጥሮ ሲሰራ በነበረው የጥበቃ ሠራተኛ እና ሁለት ግብረ አበሮቹ የተቃጣውን የዘረፋ ሙከራበማክሸፍ ወንጀል ፈፃሚዎቹ እንዲያዙ አድርጓል።


አንድ ድርጅት ካለው ሀብት ትልቁ እና ዋናው በዲስፕሊን የታነፀ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ነው፡፡ በዚህ ረገድ አቶ ተመስገን በባንኩ የተጣለበቸውን ኃላፊነት እና ዕምነት በአግባቡ በመወጣት በታማኝነት እና በተቆርቋሪነት መንፈስ ላሳዩት አርዓያነት ያለው ተግባር የባንኩ የሥራ አመራር በሁሉም የባንኩ ሠራተኞች ስም ከፍተኛ ምስጋናውን ለማቅረብ ይወዳል፡፡ ለዚህ ተግባራቸውም ባንኩ የገንዘብ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡