ሕብረት ባንክ የተገነባበትን የሕብረትና የአካታችነት መርሁን የሚያጐላለትን አዲስ መለያ እና አርማ ይፋ አደረገ፡፡ ባንኩ አዲሱን መለያ ቀርጾ ያጠናቀቀው ዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያለውን የባንኩን የጨረታ መስፈርቶች በሟሟላት ከተመረጠው ስቱዲዩኔት ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከተሰኘ ሀገር በቀል አማካሪ ድርጅት ጋር በመሆን ነው፡፡ እንደምንጊዜውም ሕብረት ባንክ እንዲህ ዓለምአቀፋዊ ብቃት ካላቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር በመሥራት ይህንን የመሰሉ ትልልቅ ፕሮጀክት ሲያሳካ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል፡፡ በተመሳሳይ ሕብረት ባንክ በቅርቡ የኮርባንኪንግ እና የኦንላይን ፐላትፎርም በራሱ የአይቲ ቡድን ማዘመኑ የሚታወስ ነው፡፡

አዲሱ የባንኩ መለያ ሕብረት ባንክ ከደንበኞቹ፣ ከአጋሮቹና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትስስር እንዲያንፀባርቅ ሆኖ የተቀረፀ ሲሆን፤ በሕብረት እና በጋራ እድገት ላይ የተመሠረተ መስተጋብር ወይም “Eco-system” ለመፍጠር ባንኩ የወሰደውን ቁርጠኝነትም ጭምር የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በእርግጥም የስኬታችን ምንጭ ደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን ናቸው፡፡ ‹‹በሕብረት እንደግ›› የሚለው የባንካችን መሪ ቃልም ለዚህ እውነት እማኝ ነውና በጐላ እና በደመቀ መልኩ መገለጥ እና መታየት ይገባዋል፡፡

ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አዲሱ የባንካችን መለያ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ከቴክኖሎጂ ጋር ያለንን ቁርኝት ከግንዛቤ ውስጥ የከተተና፣ ከዚህ በስተጀርባ ውስብስብ የሚመስሉ አያሌ ጉዳዮች በመላ የሚቃለሉበትን መንገድ የሚጠቁም ብሎም ወደፊት ለመገስገስ የምንገባውን ቃልኪዳን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ ያካበተውን የቴክኖሎጂ ብቃት፣ የደንበኞቹንና የአጋሮቹን አብሮነት እንዲሁም በፋይናንሱ ዘርፍ ያዳበረውን ልምድ በመሰነቁ የተሻለ ነገን በሕብረት ለመገንባት የሚያስችል ጠንካራ ጉልበት እንዳለው እሙን ነው፡፡

አዲሱ የሕብረት ባንክ መለያ የተለያዩ ሕብረ ቀለማትን ያካተተ ሲሆን ይህም የሕብረትን ምንነት የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ቀለማቱ ዘመናዊነትን፣ ሙያዊ ጨዋነትንና፣ መስህብን በማመላከት ዕይታን የሚስቡና በቀላሉ ተለይተው የሚታወቁ ናቸው ፡፡

የአዲሱ የባንካችን መለያ እና አርማ ፍሬ ሀሳብ ‹‹ሕብረት›› ከሚለው ስማችን የተወሰደ ሲሆን መልዕክቱም ትብብርን፣ ሕብርን፣ አብሮነትን፣ አጋርነትን፣ ቅንጅትንናመተጋገዝንየሚገልጽነው፡፡

ይኽንንምከግምትውስጥበማስገባትእንደአንድኢትዮጵያዊባንክስማችንበዓለምአቀፍደረጃ “ሕብረት ባንክ” በሚለው ስያሜ ብቻ የሚወከል ስለሆነ እንደከዚህ ቀደሙ ዩናይትድ ባንክ የሚለውን የእንግሊዝኛ ትርጓሜ እንደአማራጭ ስያሜ በቀጣይ የማንጠቀም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የአዲሱ መለያ ቃልኪዳንም (Brand Promise) “በሕብረት የተሻለ ነገን እንገነባለን” የሚል ነው፡፡ ይህም ቃልኪዳን ውስጣችንን የሚያነቃቃና ከጅምሩ የተመሰረትንለትንና አሁንም የምንጠቀምበትን መሪ ቃል (tag line) “በሕብረት እንደግ” የሚለውን በሕብረት የማደግ ዓላማ የሚያጸና ነው፡፡

በሕብረት እንደግ!