የሕብረት ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 10ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ስብሰባ እና 20 ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ስለሚካሄዱ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የ10ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ስብሰባ አጀንዳዎች

1.   የስብሰባውን አጀንዳዎች ማጽደቅ

2.   የባንኩን የተከፈለ ካፒታል ማሳደግን አስመልከቶ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

3.   የስብሰባውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

የ20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ አጀንዳዎች

1.   የስብሰባውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፣

2.   የአክሲዮን ዝውውር ማጽደቅ፣

3.   የዲሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፣ መመርመርና ተወያይቶ ማጽደቅ፣

4.   የኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥና የባንኩን

-    የሀብትና ዕዳ ሚዛን እና

-    የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣

5.   የባንኩን ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል መወሰን፣

6.   የዲሬክተሮች የቦርድ አባላትን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣

7.   የአገልግሎት ጊዜያቸውን ባጠናቀቁ የቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄድ

8.   በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ለ2018/2019 በጀት ዓመት የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፣ ክፍያቸውን መወሰን እና የስራ መመሪያ ማጽደቅ፣

9.   የስብሰባውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ፡-

§   በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከሦስት ቀናት በፊት ባንኩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ሰነድ በባንኩ ዋና መ/ቤት (በቅሎ ቤት ሜክዎር ኘላዛ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ የባንኩ አክሲዮን ክፍል) ድረስ ቀርቦ በመፈረም ሌላ ሰው ለመወከል ይችላል፡፡

§   ማንኛውም ባለአክሲዮን ለስብሰባው ሲመጣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡

§   በውል አዋዋይ የተረጋገጠና በስብሰባው በመካፈል ድምፅ ለመስጠት ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ ውክልናውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ለመሳተፍ ይችላል፡፡

 

የሕብረት ባንክ አ.ማ.

የዲሬክተሮች ቦርድ

የሕብረት ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ባካሄዱት 19ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/62/2015 መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን የመረጡ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ኮሚቴውም ባለአክሲዮኖች ጥቆማ እንዲያደርጉ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ባሳወቀው መሰረት ጥቆማዎችን ሲቀበል ቆይቷል፡፡ የጥቆማ ማቅረቢያው ጊዜ ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም አስመራጭ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/62/2015 አንቀጽ 8.2.4 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በባለአክሲዮኖች ከተጠቆሙት  መሀል ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የተቀመጡትን መመዘኛዎችን ያሟላሉ ብሎ ያመነባቸውን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕጩዎችን ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ምርጫ  በዕጩነት ያቀረበ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ 

 ለቦርድ አባልነት የተጠቆሙ ዕጩዎች ዝርዝር

 1.  አቶ አየለ በላቸው መሸሻ

2.  አቶ ጌታቸው አየለ ባልቻ

3.  አቶ ጌታመሣይ ደገፉ ወ/ሚካኤል

4.  አቶ ወሰኑ ኩመላ ግራኝ

5.  አቶ ፀጋዬ ደገፉ ወርቁ

6.  አቶ ዛፉ ኢየሱስወርቅ ዛፉ

7.  አቶ ፍቃዱ ግርማ ገብረማርያም

በልስቲ ነገሣና ልጆቹ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር / አቶአንተነህዘገየመንግስቴ/ 

9.  ወ/ሮ ጌጡ ጌታሁን ወልደጨርቆስ

10.  አቶ አለምሰገድ ከበደ መኮንን

11.  አቶ ተስፋዬ በዳዳ ሰንበታ 

12.  አቶ ሣህሌ ጥላሁን ወልደጊዮርጊስ 

 

ለቦርድ አባልነት በተጠባባቂነት የተጠቆሙ ዕጩዎች ዝርዝር

 1. የመንግስት  ቤቶች ኤጀንሲ ሠራተኞች መረዳጃ እድር /ወ/ሮአሰለፈች ደጀኔ ጩፋ/ 

2. አቶ አዱኛ ጅብሪል ወርቁ

 ሕብረት ባንክ አ.ማ.

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

አብረን ተጉዘናል፤ ሃያ ዓመታት !

ሃያ ክረምት አልፎ ፤...ሃያ መስከረም ሲጠባ ፤

ከናንተ ጋር ... ዘመን ቀይረና ል ፤
ሃያ ጊዜ ፤ አዲስ አደይ አበባን ፤
ሃያ ጊዜ ፤ አዲስ የመስቀል ወፍ ስትመጣ አይተናል ፤
ሃያ ዓመታትን ፤ ወንዞቻችን ፤ ከዘመን ጋር ሲሞሸሩ ፤
መስኩ ... በአደይ ሲያሸበርቅ ፤

አዲስ ዓመት፤ ... አዲስ በዓል ፤... አዲስ ምድር ፤ 
... አዲስ ተስፋ ፤ ሕብረት ሲፈጥሩ ፤ ... ሕብረት ባንክ ፤
ሃያ ዓመታትን ፤

... መተሳሰብ ፤ መነፋፈቅ ፤ መደጋገፍ ፤ መጠያየቅ ፤
ሕብር ሆነው ፤ ሲያንፀባርቁ ፤ ... ሕብረት ባንክ ነበር !
እንኳን አደረሳችሁ !!!

አነሆ ፤ በፍቅር እንድንቀበል ፤ ከውጭ አገር ፤ለበዓል ማድመቂያ ፤

በዌስተርን ዩኒየን ፤ በደሀብሽል ፤ ... በመኒግራም፤ በኤክስፕረስ መኒ ፤

በወርልድ ሪሚትና በሌሎችም ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል፤ የተላከሎትን ገንዘብ ፤

ከወዳጆ ወደ እጆ ሊያቀብል ፤ ሕብረት ባንክ፤ ዛሬም ከርሶ ጋር ነው !

... በባንካችን የስዊፍት ኮድ በኩል የተላኮለትን
ገንዘብም ፤ ... በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ፤ በፍጥነት መቀበል ስለሚችሉ ፤ ደስ ይለናል !

 

መልካም አዲስ ዓመት !!!

 

ሕብረት ባንክ !!!!
በሕብረት ሰርተን ፤ በሕብረት እንደግ !!!!