ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 ወይም 98/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በግልጽ ሐራጅ /ጨረታ/ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

የሐራጅ ደንቦች፣

1.   ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሠረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡

2.   በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎችና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡

3.   የሐራጅ ላይ ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ሾላ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ (ሾላ ገበያ አካባቢ) የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡

4.   ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከአበዳሪው ቅርንጫፍ ወይም ከሕግ አገልግሎት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡

5.   የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን የጨረታው አሸናፊ/ገዢው ይከፍላል፡፡

6.   ተሽከርካሪዎቹ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ስለሆነ ከቀረጥ ነፃ መብት ያለው ተጫራች ካሸነፈ እና አስፈላጊውን መመዘኛ ካሟላ ያለቀረጥ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 

7.   ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ሕግ አገልግሎት መምሪያ 011-4-70-03-15/47/69 ወይም (ሲ.ኤም.ሲ ቅርንጫፍ 011-4-47-85-64/65/66) ወይም (0116-81 12 95) ደውለው መጠየቀ ይችላሉ፡፡