Hibret-Bank-Announcement-for-Shareholders-2026-1

ለውድ የሕብረት ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

 ለውድ የሕብረት ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

 ሕብረት ባንክ አ.ማ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2021 አንቀጽ 75 እና የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2024 አንቀጽ 4 እና 29 መሰረት የሚጠበቅበትን ቅድመ-ሁኔታ በማሟላት የባንኩን የምዝገባ መግለጫ (Prospectus) አጸድቆ በነባር ባለአክስዮኖች የተያዙ አክስዮኖችን ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ማስመዝገቡ ይታወቃል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ግዑዝ አልባ ስለማድረግ በመመሪያ ቁጥር 1047/2025 በተደነገገው መሰረት የባንኩን ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ከወረቀት ወደ ኤሌክትሮኒክስ ምዝገባ ስርዓት እንዲቀየሩ (ግዑዝ አልባ እንዲደረጉ) እና በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (Central Securities Depository) እንዲመዘገቡ ያዛል። ከዚህ በኋላ በአክሲዮኖቹ ላይ የሚፈጠሩ የባለቤትነት መብቶች፣ የአክሲዮን ዝውውሮች፣ መያዣዎች እንዲሁም ሌሎች የባንኩ ውሳኔዎች ህጋዊ እውቅና የሚያገኙት በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት ስርዓት ሲመዘገቡ ብቻ መሆኑ ተደንግጓል። ሰለሆነም የባንኩ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት ስርዓት ውስጥ ትክክለኛ ምዝገባ እንዲኖራቸው ለማድረግ የግድ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማለትም የቀበሌ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ፓስፖርት፣የውጭ ሃገር ዜግነት ላላችሁ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜግነት የሰጣችሁን አገር ፓስፖርት እና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣የፋይዳ መታወቂያ (National ID)፣ የኢሜል አድራሻ እና ስልክ ቁጥር እስከ አሁን ያላሟላችሁ ባለአክስዮኖች ሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፎች በኩል መረጃ በአስቸኳይ እንድትሰጡ እናሳውቃለን።

ማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ባለአክሲዮኖች በሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት (ሕብር ታወር) 24ኛ ፎቅ በሚገኘው የአክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114-70-49-32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ሕብረት ባንክ አ.ማ

Similar Posts