ሕብረት ባንክና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በአካታች የፋይናንስ ስርዓት ዝርጋታ ዙርያ ውይይት አካሄዱ


የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገብረእግዚአብሔር ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ሙፋሪያት ካሚል ጋር በአካታች የፋይናንስ ስርዓት ዝርጋታ ዙርያ ወይይት አካሂደዋል፡፡
ሕብረት ባንክ የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ አስቀድሞ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ በአጋርነት እየሰራ ያለ ጠንካራ ባንክ ሲሆን ፤ ይህን ትብብር የበለጠ ለማጎልበት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከክብርት ሚኒስትሯ ጋር በውጪ ሀገር የስራ ስምሪት ፣ በክህሎት እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ ላይ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል፡፡ በሥራ ፈጠራ ስነ ምህዳሩ ላይ አካታች የፋይናንስ ስርዓት በመዘርጋት የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥም በቅንጅት ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!