News regarding Hibret Bank's excellent performance

ሕብረት ባንክ በተጠናቀቀው የ2025/26 የበጀት ዓመት አመርቂ ውጤት አስመዘገበ፡፡

ሕብረት ባንክ በተጠናቀቀው የ2025/26 የበጀት ዓመት አመርቂ ውጤት አስመዘገበ፡፡

ሕብረት ባንክ አ.ማ በተጠናቀቀው የ2025/26  የበጀት ዓመት በዋና ዋና የሥራ አፈጻጸም መመዘኛዎች ከመቼውም ጊዜ የላቀ አመርቂ ውጤት በማግኘት የተሳካ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡

የሕብረት ባንክ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ  አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔር የበጀት ዓመቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት የተገኘው ውጤት ለባንኩ የከፍታ ጉዞ ጅማሮ መሆኑን ገልጸው  ለዚህ ስኬት ከባንኩ ጎን የቆሙ ታማኝ ደንበኞችን፣ ክቡራን ባለአክሲዮኖችን፣ የቦርድ ዳይሬክተሮችን፣ የሥራ አመራሮችን  እና መላው የባንኩ ሠራተኞችን አመስግነዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ የ2026/27 የበጀት ዓመት ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረው የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው የባንኩ አመራሮች እና ሠራተኞች አዲስ የተቀረፀውን የአምስት ዓመት ኮርፖሬት ስትራቴጂ ከዚህ በበለጠ ትጋት በመተግበር ባንኩ የሰነቀውን ራዕይ እንዲያሳኩ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts