ሕብረት ባንክ አመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔውን በስኬት አጠናቀቀ፡፡















ሕብረት ባንክ አመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔውን በስኬት አጠናቀቀ፡፡
ሕብረት ባንክ የ2024/2025 አመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔውን ‘’ማዕበሉን ተቋቁመን በአላማ እየተመራን በፅናት እናሸንፋለን’’ በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 17 እና 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አካሂዷል፡፡
በጉባዔው ላይ የሕብረት ባንክ የዲሪክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ተሰማ ወቅቱ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን እንደሁልጊዜው የዲሪክተሮች ቦርድ፣ ማኔጅመንቱና ሠራተኛው እጅ ለእጅ በመያያዝ እንደ አንድ ቤተሰብ ለጋራ ስኬት በመስራትና ለደንበኛው የላቀ አገልግሎት በመስጠት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና በዘርፉ ተወዳደሪ ሆኖ ለመቀጠል መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ አቶ መስፍን አክለውም ሕብረት ባንክን ወደሚገባው ከፍታ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የዲይሬክተሮች ቦርድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
የባንኩ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ተስፋዬ በበኩላቸው የበጀት አመቱ ከቀደሙት አመታት በተለየ ትልቅ ርብርብን የጠየቀ ፈታኝ የሥራ ዘመን እንደነበር ገልፀው ያጋጠሙ ችግሮችን ለመቀልበስ የዲሪክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አመራሩና ሰራተኛው በሕብረት ሆነው በመስራት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ለአንድ አላማ በአንድነት መንቀሳቀስ ከተቻለም የማይፈታ ችግር እንደሌለና በቀጣይ አመትም ይህን ውጤት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በሥራ አመራር ጉባዔው ላይ በ2024/2025 የላቀ የስራ አፈፃፀም የነበራቸው ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች ተሸልመዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚሁ አመታዊ የስራ አመራር ጉባዔ ላይ የባንኩ ዲሪክተሮች ቦርድ አመራር አባላት፣ የባንኩ ሥራ አመራር አባላት፣ የዋናው መስሪያ ቤት እና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እንዲሁም የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!