ሕብረት ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስስ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡




ሕብረት ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስስ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ሕብረት ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስስ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መሥርያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡
ሕብረት ባንክን በመወከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ አስራት አረጋ ሕብረት ባንክ በሀገራችን የባንክ ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎችን በራስ አቅም በማበልፀግ ፈርቀዳጅና በእውቀት ሽግግሩም ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀው ከካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ጋር የተደረሰው ስምምነትም የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ፣ የቁጠባ ባህልን በማበረታትና የብድር አገልግሎትን በማሳለጡ በኩል የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብረሃም ጥላሁን በበኩላቸው የባንክና የፊንቴክ አጋርነት ጊዜው የሚጠይቀው መሆኑን ገልፀው በሀገራችን ግዙፍ ከሆኑት ባንኮች አንዱ ከሆነውና በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ አመኔታ ካለው ከሕብረት ባንክ ጋር የተደረሰው ስምምነትም በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ረገድ ወቅቱን የዋጀና ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!