ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክርበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ::

ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክርበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ::
ሕብረት ባንክና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የባንኩ አመራሮች ይህን ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጋር መክረዋል፡፡
የባንኩ አመራሮች ለአዲሱ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት ለቤተክርስትያኒቱ ያደረሱ ሲሆን በወቅቱም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!