Hibret Bank first-quarter performance review 01

ሕብረት ባንክ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ!

ሕብረት ባንክ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ!

ሕብረት ባንክ የ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማውን በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የመሰብሰብያ አዳራሽ ጥቅምት 13 እና 14 ቀን 2019 ዓ.ም. አካሂዷል፡፡  

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ባንኩ በሁሉም የአፈፃፀም መመዘኛዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡

ለውጤቱ መገኘት በሁሉም ደረጃ የተቀናጀ ጥረት መደረጉ አስተዋዕኦ እንደነበረው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ባንኩ በዓመቱ ያስቀመጠውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ሁሉም የባንኩ ሰራተኛ የተጠናከረ ጥረት ማድረግ እንዳለበትም መመሪያ ተላልፏል፡፡ 

በሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማው ላይ የዋና መሥሪያ ቤት እና የዲስትሪክት ማኔጅመንት አባላት  ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts