Platinum Taxpayer Award

ሕብረት ባንክ የኘላቲንየም ደረጃ ግብር ከፋይ ሽልማት ተሸላሚ ሆነ

ሕብረት ባንክ የኘላቲንየም ደረጃ ግብር ከፋይ ሽልማት ተሸላሚ ሆነ!

ሕብረት ባንክ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ካገኘው ገቢ በታማኝነት ግብር በመክፈል በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ተኛው ዙር የሀገር አቀፍ ታማኝ ግብር ከፋዮች የእወቅናና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት የኘላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ 

የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔር ሽልማቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ የተቀበሉ ሲሆን ሕብረት ባንክ ይህን መሰል ሽልማቶችን ሲያገኝ ለሰባተኛ ጊዜ ነው፡፡ 

ሕብረት ባንክ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ሀገርና ሕዝብን የሚጠቅሙ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በታማኝ ግብር ከፋይነት ያገኘው ይህ ሽልማትም  በሕብረት እንደግ በሚለው መርሁ ለሚታወቀው ባንካችን እውቅና የሰጠ ነው፡፡  

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ

Similar Posts