Hibet-Bank-SemiAnnual-1

ሕብረት ባንክ የግማሽ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ግመገማውን አካሄደ!

ሕብረት ባንክ የግማሽ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ግመገማውን አካሄደ!

ሕብረት ባንክ የ2018 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማውን በባንኩ ዋና መስርያ ቤት የመሰብሰብያ አዳራሽ ጥር 1 እና ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. አካሂዷል፡፡ 

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ባንኩ በሁሉም የአፈፃፀም መመዘኛዎች አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡ 

ለውጤቱ መገኘት በሁሉም ደረጃ የተቀናጀ ጥረት መደረጉ አስተዋዕኦ እንደነበረው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ባንኩ በዓመቱ ያስቀመጠውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ሁሉም የባንኩ ሰራተኛ የተጠናከረ ጥረት ማድረግ እንዳለበትም መመሪያ ተላልፏል፡፡ 

በግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማው ላይ የሕብረት ባንክ የማኔጅመንት አባላት እና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts