የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ 

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየይዞታ መብት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.አቶ ቶማስ ጀማልአቶ ቶማስ ጀማልጎፋ ማዞሪያአዲስ አበባ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 09፣ የቦታ ስፋት 37.71 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት፤ 
 
 
ጎፋ09/2330/2001
 
3,537,267.00
የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 
2.አቶ ተሰማ አያኖ ሻመናአቶ ተሰማ አያኖ ሻመናለቡ ላፍቶ 
አዲስ አበባ፤ንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ወረዳ 01፤የቦታ ስፋት 175 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤት
 AA00008011211820,346,579.00የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5:00 እስከ 6:00 ሰዓት
3.ወ/ሮ ሶፋ መሃመድ የሻውሐሮት ፋሚሊ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ቦሌ ቡልቡላኦሮሚያ ክልል፣ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ፣የቦታ ስፋት 5,000 ካ.ሜ፣ለማኑፋክቸሪንግ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት መጋዘኖች እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል G+1 ቤት 
B/M/G/K/L/I/55/2001
64,916,824.00የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 
4.አቶ ሃንበሳ ብርካ ከላቾአቶ ሃንበሳ ብርካ ከላቾሻሸመኔሻሸመኔ ከተማ፣ቀበሌ አቦስቶ፣የቦታ ስፋት 190 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትB/01103,921,002.00የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 
5.አቶ ገለታ ቁምቢ ሮባአቶ ዱቤ ቁምቢ ሮባቡሌሆራ ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ቡሌሆራ ከተማ፣ቀበሌ B/Q የቦታ ስፋት 320 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትBH/2052/D.255/20133,522,780.00የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 
.ወ/ሮ መሰረት ጳውሎስ ሙዳቡሌሆራ ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ቡሌሆራ ከተማ፣ቀበሌ B/Q የቦታ ስፋት 320 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትBH/5051/M.218/20153,208,768.00የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት
6.አቶ ጫኔ ዘለቀ መንግስቱወ/ሮ ዘቢደር አድማሱ ገድፍአዴትጎጃም፣አዴት ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 250 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትከአገ/112466/12648,196.00የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
7.አቶ ተዋሰኝ ሙሉ ተፈሪአቶ ተዋሰኝ ሙሉ ተፈሪአዴትጎጃም፣አዴት ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 250 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትከአገ/1189/2007684,728.00የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት
8.አቶ ባየህ እንዳለማው ገላውአቶ ሳለአምላክ አትክልት በቀለሽንዲጎጃም፣ቡሬ ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 150 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት14962/2013884,075.00የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
አቶ እንዳለማው ገላው ሞሴሽንዲጎጃም፣ሽንዲ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 175 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትሸማ/6359/መ/ሮ/1909,205.00የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት 
9.አቶ ተመስገን መልካሙ ዳምጤአቶ ተመስገን መልካሙ ዳምጤቴዎድሮሰጎንደር ከተማ፣ማራኪ ክፍለ ከተማ፣ቀበሌ 18፣የቦታ ስፋት 1150 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለንግድ የሆነ ህንፃ20516/1430,296,943.00የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች(የጨረታው አሸናፊ)ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲያፀድቀው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. በተራ ቁጥር 1 እና 2  የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡በተራ ቁጥር 3-5 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚካሔደውንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡ከተራ ቁጥር 6-8 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚካሄደው ባህርዳር ከተማ፣ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና(ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ነው፡፡በተራ ቁጥር 9 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ ደግሞ ጎንደር ከተማ በሚገኘው የባንኩ ቴዎድሮስ ቅርንጫፍ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
  5. በተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሰውን ንብረት  ብቻ ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  7. ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ወይም ከቅርንጫፎቹ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ ጎፋ ማዞሪያ ቅርንጫፍ፡ 0114 70 23 05 ፣ ለቡ ላፍቶ ቅርንጫፍ: 0114 19 90 61፣ ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ: 0114  71 40 78/91፣ ሻሸመኔቅርንጫፍ፡ 046 11 10 04 36፣ ቡሌሆራ ቅርንጫፍ: 0464 43 16 48፣ አዴት  ቅርንጫፍ: 058 338 10 72፣ ሽንዲ ቅርንጫፍ: 058 449 07 64፣ ቴዎድሮሰ ቅርንጫፍ፡ 058 111 23 39 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ: 0114 70 03 15 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts