የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ 

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.ወይ/.ሳሚያ አብዱልቃድር ጎዱአቶ ብርሀኑ አበራ ሀይሌአራት ኪሎ አዲስ አበባ ከተማ፣ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 09፣ የቦታ ስፋት 250 ካ/ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤት 
 
 
 
ለ/ኩራ9/36/4/45933/0383/9/00
 
 
 
29,187,018.00
ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
2.ወ/ሮ አልማዝ አጥላው ዘመድኩንወ/ሮ ነፃነት ደግፌሳጉሬ 
አርሲ፣ቦቆጂ ቀበሌ B/Q የቦታ ስፋት 175 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለንግድ የሆነ  ቤት
2391/2015 
1,993,540.00 
ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
3.ወ/ሮ እየሩስ ገዳሙ አየለአቶ አበባው ዓለም ገድፍፈለገ ህይወትጎጃም፣አዴት ከተማ፣ቀበሌ 05፣የቦታ ስፋት 150 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት 
ከአገ/113207/13
1,332,915.00ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
አቶ አበባው ዓለም ገድፍፈለገ ህይወትሞጆ ጎጃም፣አዴት ከተማ፣ቀበሌ 05፣የቦታ ስፋት 150 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤትከአገ/113208/13 
1,278,908.00
ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡ 
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ ደግሞ የሚካሄደውንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡በተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚካሄደው ባህርዳር ከተማ፣ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና(ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ነው፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  7. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶች  ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ አራት ኪሎ: ቅርንጫፍ 0111 26 43 62፣ ሳጉሬ ቅርንጫፍ፡ 0223 38 08 86፣ ፈለገ ህይወት ቅርንጫፍ: 0583 20 89 69ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts