የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ 

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.አቶ አሊ አህመድ የሱፍወ/ሮ እስከዳር በቀለ ገ/ሚካኤልበሻሌአዲስ አበባ ከተማ፣ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ወረዳ 08፣ የቦታ ስፋት 356 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ አፓርትመንት ቤት 
 
AA0000408004570309901
 
 
30,877,766.00
ታህሳስ  22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
2.አቶ ቶማስ ጀማልአቶ ቶማስ ጀማልጎፋ ማዞሪያ 
አዲስ አበባ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 09 ፣የቦታ ስፋት 37.71 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ኮንዶሚኒየም ቤት፤
ጎፋ09/2330/2001 3,537,267.00ታህሳስ  22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
3.አቶ አህመድ ሁሴን መሀመድአቶ አህመድ ሁሴን መሀመድሎጊያ-ሰመራአፋር ክልል፣ሰመራ ሎጊያ ከተማ፤ቀበሌ ሎጊያ፣ የቦታ ስፋት 640 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ  የሆነ  ቤትሠ/ሎ/ከ/አ/377/2013 799,195.00ታህሳስ  22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
4.አቶ  አሳዬ አድማሱ መንታአቶ  አሳዬ አድማሱ መንታቦዲቲቦዲቲ ከተማ፣ሶዶ በር ክፍለከተማ፣ቀበሌ ሶዶ በር፣ የቦታ ስፋት 700 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለንግድ የሆነ ቤትበማቤ/መ/ል/አስ/ር/12/9105,057,498.00ታህሳስ  22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ  ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
5.አቶ አቡሳድ ነሻ አህመድአቶ ነሻ አህመድ አልይሕብር ታወርአዳማ ከተማ፣ቀበሌ 03፣የቦታ ስፋት 1709 ካ.ሜ የሆነ ለመጋዘን አገልግሎት የሚውል2110/200017,183,808.00ታህሳስ  23 ቀን 2018  ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
6.ወ/ሮ ሶፋ መሃመድ የሻውሐሮት ፋሚሊ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ቦሌ ቡልቡላኦሮሚያ ክልል፣ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ፣የቦታ ስፋት 5,000 ካ.ሜ የሆነ ለማኑፋክቸሪንግ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት መጋዘኖች እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል G+1 ቤትB/M/G/K/L/I/55/200164,916,824.00ታህሳስ  24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች(የጨረታው አሸናፊ)ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲያፀድቀው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች  ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡የሌሎች ንብረቶች ሐራጅ ደግሞ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ይካሄዳል፡፡
  5. በተራ ቁጥር 5 እና 6 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች  ብቻ ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ወይም ከቅርንጫፎቹ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- በሻሌ ቅርንጫፍ፡ 0116 67 08 40፣ ጎፋ ማዞሪያ ቅርንጫፍ፡ 0114 70 23 05 ፣ ሎጊያ ሰመራ ቅርንጫፍ0335 50 00 15/27፣ ቦዲቲ ቅርንጫፍ :0465 59 08 62፣ ሕብር ታወር ቅርንጫፍ 0115 57 54 47 ፣ ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ: 0114  71 40 78/91 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ: 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts