የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.አቶ ብሩክ ባርሴ ሙሉጌታ አቶ ብሩክ ባርሴ ሙሉጌታዲላዲላ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 199.687  ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤት 
 
SN003010415140
 
 
1,547,698.00
ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
2.አዱራ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ/አዱራ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ/ጋምቤላ 
ጋምቤላ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 1434 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለንግድ የሆነ ቤት
34941/20129,026,345.00ጥር 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ስዓት
3.ወ/ሮ ምላሽ አብርሃ በርሄወ/ሮ ምላሽ አብርሃ በርሄባሮ ማዶጋምቤላ ከተማ፤ቀበሌ 04፣የቦታ ስፋት 770 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለንግድ የሆነ ቤት231113/012,587,675.00ኅዳር 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
ወ/ሮ ምላሽ አብርሃ በርሄወ/ሮ ምላሽ አብርሃ በርሄባሮ ማዶጋምቤላ ከተማ ቀበሌ 05፣የቦታ ስፋት 400 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት32654/09650,970.00ጥር 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8:00 እስከ 9:00 ሰዓት
4የሱፍ መሐመድ አሊ(አሊፍ የምግብ ማምረቻ ኮምፕሌክስ)አቶ ተረፈ ደሳለኝ መኩሪያ 
ቴዎድሮሰ
ጎንደር ከተማ፣አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 20፣የቦታ ስፋት 3000 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለኢንደስትሪ የሆነ ግንባታኢፓልኮ/ጎን/56/1217,033,883.00ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች (የጨረታው አሸናፊ) ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲያፀድቀው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. በተራ ቁጥር 1 - 3 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡ በተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ ደግሞ ጎንደር ከተማ በሚገኘው የባንኩ ቴዎድሮስ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ይካሔዳል፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  6. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ወይም ከቅርንጫፎቹ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  8. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- ዲላ ቅርንጫፍ፡ 0463 31 13 27 ፣ ባሮ ማዶ ቅርንጫፍ፡ 0471 51 91 58፣ ጋምቤላ ቅርንጫፍ; 0475 51 08 28; ቴዎድሮስ ቅርንጫፍ፡ 0581 11 23 39 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ: 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts