የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
| ተራ ቁ. | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የንብረቱ የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| 1. | አቶ እስክንድር ብርሃኔ ግደይ | ወይ/ ሳራ ኪዳኔ ወ/ማርያም | ኢምፔርያል | አዲስ አበባ ከተማ፣ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 06፣የቦታ ስፋት 278 ካ/ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ G+2 ቤት | ቦሌ6/2/6/7/27630/16062/02 | 50,511,632.00 | የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 2. | አቶ ተማም ሺፋ | አቶ ተማም ሺፋ | መናኸሪያ ጅማ | ጅማ ከተማ፣ቦሬ ቀበሌ፣የቦታ ስፋት 357 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | 4419/2014 | 4,284,395.00 | የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 3. | መኪያ እና እስማኤል የዶሮ እርባታ ሽርክና ማህበር | ወይ/ መኪያ ሲራጅ | መናኸሪያ ጅማ | ጅማ ከተማ፣ግንጆ ጉዱሩ ቀበሌ፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | 5430/2014 | 2,747,220.00 | የካትት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት |
| 4. | ወይ/ ሀድያ አባተ | ወይ/ ሀድያ አባተ | ኒውላንድ ጋምቤላ | ጋምቤላ ከተማ፣ቀቤለ 05፣የቦታ ስፋት 411 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | 36797/15 | 3,391,260.00 | የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተውን ንብረት ብቻ ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ የሌሎች ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማናቸውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ ኢምፔርያል ቅርንጫፍ 0116 60 94 16፣ መናኸሪያ ጅማ ቅርንጫፍ፡ 0472 11 99 42፣ ኒውላንድ ጋምቤላ ቅርንጫፍ፡ 0475 51 27 02 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ፡ 0114 70 03 15/47 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!