የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍየሰሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪ አይነትየስሪት ዘመንየሻንሲ ቁጥርየሞተር ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ (ተ.ዕ.ታ.ን ሳይጨምር) ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.ሬድሮክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ሬድሮክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ቦሌ መድሃኒአለም አአ-03-B16263 
ጃፓን- ሊንከሊን-አውቶሞቢል
 
2020/እ.አ.አ
 
5LMJJ2LT7LEL06793
LEL0679315,650,000.00ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
2.ሬድሮክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ሬድሮክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ቦሌ መድሃኒአለም 
አአ-03-B15111
እንግሊዝ-ሬንጅሮቨር- የመስክ ተሽከርካሪ 
2020/እ.አ.አ
SALGA2BU1LA407727LA40772715,350,000.00ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ተሽከርካሪዎቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
  3. ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደአገር ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ 
  4. የመኪናዎች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  5. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  7. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ 0115 57 37 72/0114 70 41 03 ወይም 0114 70 03 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts