Mekedonia and Hibret Bank 01

የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ለመቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በዓመቱ የ6.2 /ስድስት ሚልዮን ሁለት መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ለመቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በዓመቱ የ6.2 /ስድስት ሚልዮን ሁለት መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በመቄዶንያ የሕብረት ባንክ ቀን ሆኖ በተሰየመው ጳጉሜን 4 ሕብረት ባንክ ከሠራተኞቹ ያሰባሰበውን የገንዘብ ድጋፍ ለመቄዶንያ አረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አበረከተ፡፡

ሕብረት ባንክ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ እየተከናወነ በነበረው የማዕከሉ ህንፃ ግንባታ ማስጨረሻ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ-ግብር እና በጳጉሜ 4/2018 በሕብረት ባንክ ቀን ከሠራተኞቹ ያሰባሰበውን ጨምሮ በአጠቃላይ በአመቱ የስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ (6,200,000) ብር የገንዘብ ድጋፍ ለመቄዶንያ አበርክቷል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ የሕብረት ባንክ ቺፍ ማርኬቲንግ እና ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ ደረጀ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት በየዓመቱ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ በመቄዶንያ መገኘት ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸው ዕለቱ የተሰባሰበውን የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመቄዶንያ የምናበረክትበት ብቻ ሳይሆን ደግነትን፣ ለማሕበረሰቡ መቆምን የምናጠናክርበት እና እንደባሕል ወጋችን የታላላቆችን ምርቃት ለመጪው ዘመን የምንቀበልበት ጭምር ነው ብለዋል፡፡ የመቄዶንያ መስራች እና መሪ የክብር ዶ/ር ቢንያም በለጠ በበኩላቸው ለተደረገው ድጋፍ ሕብረት ባንክን እና ሠራተኞቹን አመስግነዋል፡፡

በአባቶች ምርቃት የተጀመረውን መርሃ-ግብር የባንኩ የሥራ አመራሮች እና የመቄዶንያ አባላት ታድመውበታል፡፡  

ሕብረት ባንክ እና ሠራተኞቹ ላለፉት ስድስት ዓመታት ለመቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በጥቅሉ ከ24 ሚልዮን (24,000,000) ብር በላይ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts