የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሕባ008/2018
ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትናነት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተሽከርካሪው አይነት | ታርጋ ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የተሽከርካሪ ሞዴል | የተሰራበት ዘመን | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
| 1 | አውቶሞቢል ኮሪያ ሀዩንዳይ ቱክሰን | አ.አ03-B01022 | TMAJ3812HLJ061154 | G4FG-LZ561825 | Tucson | 2019 | 3,450,000.00 | አዲስ አበባ ሰን ጋተራ በሚገኘው አዲሱ የባንኩ ህብር ታወር ህንጻ ጊቢ ውስጥ |
በመሆኑም
- ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተገለጹት አድራሻዎች በአካል በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን ይህ ሳይገለጽ ቢቀር ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ባንኩ ተጨማሪ 15% ተ.እ.ታን በመደምር የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ደግሞ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስር ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰአት በዋናው መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ ካፍቴሪያ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ባንኩ ንብረቶቹን በገዢው ስም ለማዘዋወር ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል፡፡
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 562 10 24 ወይም 0114 16 97 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!