የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሕባ009/2018

ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትናነት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች (የባንክ አክሲዮኖች) ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

.የንብረቱ ዓይነትየባለቤትነት መታወቂያ ቁጥር/ የሼር ቁጥርየአክሲዮኑ ባለቤት /Certificate Issuerየጨረታ መነሻ ዋጋ በብር
1የባንክ አክሲዮኖች/ሼርAAG7188፣ AAI07188አንበሳ ባንክ አ.ማ  2,914,850.05
2የባንክ አክሲዮኖች/ሼር6962ወጋገን ባንክ አ.ማ    764,000.00
3የባንክ አክሲዮኖች/ሼር6955፣9412፣ 08167፣ 10714፣ 12733፣ 13158፣ 14204፣ 15179ወጋገን ባንክ አ.ማ  1,200,000.00
4የባንክ አክሲዮኖች/ሼር09927ብርሃን ባንክ    207,000.00
5የባንክ አክሲዮኖች/ሼር19277፣ 19037አንበሳ ባንክ አ.ማ  2,422,198.80
6የባንክ አክሲዮኖች/ሼር007456አንበሳ ባንክ አ.ማ411,774.00

በመሆኑም

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን ይህ ሳይገለጽ ቢቀር ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ባንኩ ተጨማሪ 15% ተ.እ.ታን በመደምር የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
  3. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ደግሞ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስር ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
  4. ተጫራቾች ንብረቶቹን/አክሲዮኖቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የባንክ አክሲዮን ሽያጭ ዝውውርን በተመለከተ የወጡ ህጎች እና መምሪያዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  6. ጨረታው ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰአት በዋናው መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ ካፍቴሪያ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ባንኩ ንብረቶቹን/አክሲዮኖቹን በገዢው ስም ለማዘዋወር ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 562 10 24 ወይም 0114 16 97 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts