የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሕባ/006/17
ሕብረት ባንክ ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ አይነት የወንድና የሴት ጥበቃ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | ዝርዝር መግለጫ | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
| 1. | ብትን ጨርቅ (ሱፍ) የጨርቅ ቀለም ፐርፕል | በሜትር | 1,659 | |
| 2. | ብትን ጨርቅ (ሱፍ) የጨርቅ ቀለም ግሬይ | በሜትር | 1,659 | |
| 3. | ሸሚዝ ፈካ ያለ ውሃ ሰማያዊ ቀለም | በቁጥር | 948 | |
| 4. | ከረቫት (ለወንድ) | በጥንድ | 840 | |
| 5. | ከረቫት (ለሴት) | በቁጥር | 108 |
ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መግዛት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች እስከ መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- Tተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከህብረት ባንክ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 467 3208 ወይም +251 11 470 6541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡